Amharisch

አምነስቲ ኢንተርናሽናል

የጥገኞች የምክር አገልግሎት በቩርዝቡርግ

ስለ እኛ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ : ዓለም አቀፋዊ እና ከበፖለቲካ ነፃ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ነው:: አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጭቆና ምክንያት ከሀገራቸዉ ተሰደው በጀርመን ሀገር የሚገኙ ስደተኞችን ይረዳል::

አገልግሎታችን

በጀርመን ሀገር ውስጥ የጥገኝነት ሂደት ላይ መረጃ እና ምክር እንሰጣለን : በፌዴራል ጥገኝነት ቢሮ (BAMF) የመጀመሪያ ቃለ መጠይቅ ዝግጅት እገዛ እናደርጋለን : ከተለያዩ ቢሮዎች ወይም ከፌዴራል ጥገኝነት ቢሮ (BAMF) የሚደርስዎትን ደብዳቤዎች ገለፃ እናደርጋለን :: በተጨማሪም ለፌዴራል ጥገኝነት ቢሮ የመልስ ጹሁፎዎች ላያ እንረዳዎትአለን:: በተጨማሪም በአገሮዎት ላያ ሰላለዉ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ለጠበቃዎት እና ለእርስዎ መረጃ እንሰጣለን::

አድራሻችን

በስደተኞች ካምኘ Veitshöchheimer Str. 100 ቩርዝቡርግ ለሚገኙ ሮብ ከ 19 እስከ 20.30 ሰዓት በካሪታስ (Caritas) ህንፃ

ከስደተኞቸ ካምኘ ውጭ ለሚገኙ ስደተኞች በኢሜል አድራሻችን asylberatung@amnesty-wuerzburg.de

ወይም የአደጋ ጊዜ ስልካችን +49 (0)175-1253224 መጠቀም ይችላሉ::

3. Dezember 2018